Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ከሀንጋሪ ቡዳፔስት ወደ አዲስ አበባ ጉዞ ጀምሯል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ ከሀንጋሪ ቡዳፔስት ወደ አዲስ አበባ የሚያደርገውን ጉዞ ዛሬ ምሽት ጀምሯል ።

የልዑካን ቡድኑ አባላት ጀርመን ፍራንክፈርት ትራንዚት ካደረጉ በኋላ ማክሰኞ ንጋት 11:55 ላይ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንደሚደርሱ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳተፈው ልዑክ ነገ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲድረስም አቀባበል እንደሚደረግለት የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

ለአትሌቲክስ ልዑኩ ነገ ነሐሴ 23 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 12 ጀምሮ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል ይደረጋል ተብሏል።

በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ 2 ሰዓት የሚደረገውን አቀባበል ቀጥሎ አትሌቶቹ በአውራ ጎዳናዎች በመዘዋወር ከህዝቡ ጋር ደስታቸውን እንደሚገልጹም ተመልክቷል።

በውድድሩ ኢትዮጵያ 2 ወርቅ ፣4ብርና 3 ነሃስ ሜዳሊያዎችን በማግኘት ከዓለም 6ኛ ከአፍሪካ ደግሞ 2ኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቋ ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.