Fana: At a Speed of Life!

ሳዑዲ ዓረቢያ በተጨማሪ እሴት ታክስ ላይ ሶስት እጥፍ ጭማሪ ልታደርግ ነው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 3 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ሳዑዲ ዓረቢያ በኮሮና ቫይረስ የተጎዳውን ኢኮኖሚ ለመደገፍ በተጨማሪ እሴት ታክስ ላይ ሶስት እጥፍ ጭማሪ እንደምታደርግ አስታወቀች።

በዚህም የተጨማሪ እሴት ታክሱ ከሰኔ ወር መጨረሻ ጀምሮ ከ5 በመቶ ወደ 15 በመቶ ከፍ ይላል ነው የተባለው።

የሃገሪቱ ገንዘብ ሚኒስትር ሞሃመድ አል ጀዳን እርምጃው ከባድ ቢሆንም የተረጋጋ ኢኮኖሚን ለመፍጠርና ኮሮና ቫይረስ የሚያስከትለውን ተፅዕኖ ለመቋቋም አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

እርምጃው ሃገሪቱ በአመቱ የመጀመሪያ ሶስት ወራት ከፍተኛ የበጀት ጉድለት ካጋጠማት በኋላ የተወሰደ ነው ተብሏል።

በነዳጅ ምርቷ ላይ የተንጠለጠለው ኢኮኖሚዋም ኮሮና ቫይረስ ባስከተለው ተፅዕኖ ሳቢያ ክፉኛ መጎዳቱ ይነገራል።

የሃገሪቱ ማዕከላዊ ባንክም ባለፈው መጋቢት ወር ላይ የውጭ ምንዛሪ ክምችት በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱን አስታውቆ ነበር።

መንግስት ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጭማሪው ባለፈም እስካሁን ለዜጎቹ ይሰጥ የነበረውን የድጎማ ገንዘብ ከያዝነው ወር መጨረሻ ጀምሮ እንደሚያቋርጥ ገልጿል።

ሳዑዲ ዓረቢያ ተጨማሪ እሴት ታክስን በነዳጅ ምርቷ ላይ የተንጠለጠለውን ኢኮኖሚዋን ለመደገፍ በሚል ከሁለት አመታት በፊት ተግባራዊ ማድረግ መጀመሯ የሚታወስ ነው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.