Fana: At a Speed of Life!

ለአትሌቲክስ ልዑካን ቡድኑ የሽልማት ስነ-ስርዓት በብሔራዊ ቤተ-መንግስት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለተሳተፈው የአትሌቲክስ ልዑክ ቡድን የዕውቅናና የሽልማት ስነ-ስርዓት በብሔራዊ ቤተ-መንግስት ተካሂዷል።

በዕውቅናና የሽልማት ስነ-ስርዓርቱ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጀላ መርዳሳን ጨምሮ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ፣ የአትሌቲክስ ልዑካን ቡድኑ አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የወርቅ ሜዳልያ ላመጡ አትሌቶች አንድ ነጥብ 5 ሚሊየን ብር፣ የብር ሜዳልያ ላመጡ 1ሚሊየን ብር እና የነሐስ ሜዳልያ ላመጡ 700ሺህ ብር ተበርክቷል።

የወርቅ ሜዳልያ ላስገኙ አሰልጣኞች 750ሺህ ብር፣ የብር ሜዳልያ ላስገኙ አሰልጣኞች 500ሺ ብር፣ የነሐስ ሜዳልያ ላስገገኙ አሰልጣኞች 350ሺህ ብር ሽልማት ተሰጥቷል።

በተጨማሪም ተሳታፊ አትሌቶች ከ50ሺህ ብር አንስቶ እንደየውጤታቸው የገንዘብ ሽልማት አግኝተዋል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ለሽልማቱ በአጠቃላይ 16 ሚሊየን 950 ሺህ ብር ወጪ ማድረጉም ነው የተገለጸው።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.