Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል የእንስሣት ሃብት ልማቱን ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2016 በጀት አመት በኦሮሚያ ክልል 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ሰው ሰራሽ የእንስሣት ማዳቀል ስራ በመስራት የእንስሣት ሃብት ልማቱን ምርታማነት ለማሳደግ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡

በክልሉ አርሲ ዞን ሌሙና ቢልቢሎ ወረዳ የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ ስራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር የፌዴራልና የክልል የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ተካሂዷል።

የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌቱ ገመቹ በዚሁ ወቅት÷ የግብርናውን ሴክተር ለማዘመን በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በ2016 በጀት አመት በኦሮሚያ ክልል 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ሰው ሰራሽ የእንስሣት ማዳቀል ስራ በመስራት የእንስሣት ሃብት ልማቱን ምርታማነት ለማሳደግ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አስራት ጤራ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ የአርሲ ዞን ከሰብል ልማት በተጨማሪ በእንስሣት ሃብት ልማት ላይ እየተሰራ ያለውን የሌማት ትሩፋት ዕቅድ ለማሳካት ትልቅ ተነሳሽነትን ይፈጥራል ብለዋል።

ከስራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ በተጨማሪም በአርሲ ዞን በእንስሳት ሃብት ልማት ላይ የተሰሩ ምርጥ ተሞክሮዎች እንደተጎበኙ የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.