Fana: At a Speed of Life!

ዋልያዎቹ ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ካይሮ ገብተዋል

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አባላት ከግብፅ አቻቸው ጋር የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ መርሐ ግብርን ለማከናወን ካይሮ ገብተዋል፡፡

የብሄራዊ ቡድኑን ተጫዋቾች እና አመራሮችን የያዘው ልዑክ ከ3 ሰዓታት በላይ በረራ በኋላ ካይሮ በሰላም መግባቱን የፌዴሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች ቀደም ሲል ባደረጉት ጨዋታ ዋሊያዎቹ በዳዋ ሆጤሳ እና ሽመልስ በቀለ ግቦች ከጨዋታ ብልጫ ጋር 2 ለ 0 ማሸነፋቸው ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጂ  የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከጊኒ ጋር በደርሶ መልስ መሸነፉን ተከትሎ ከአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ ውጪ ሆኗል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.