Fana: At a Speed of Life!

የማንቼስተር ዩናይትድ ዋጋ በ500 ሚሊየን ፓውንድ ዝቅ ማለቱ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የላንክሻየሩ ክለብ ማንቼስተር ዩናይትድ የሽያጭ ዋጋው በ500 ሚሊየን ፓውንድ ዝቅ ማለቱ ተገልጿል፡፡

የክለቡ ዋጋ በአሜሪካው የኒዎርክ የአክሲዮን ሽያጭ በ500 ሚሊየን ፓውንድ ወይም በ628 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ዝቅ ማለቱ ተጠቅሷል፡፡

ክለቡ በአርሰናል ከተሸነፈ በኋላ መልበሻ ክፍል ውስጥ አለመግባባቶች ተፈጥረው እንደነበር የተዘገበ ሲሆን ፥በተለይም ክለቡ ከፍተኛ የገንዘብ ዝውውር የከፈለባቸው ተጫዋቾች ጥሩ አቋም አለማሳየታቸው አለመግባባቱን እንዲፈጠር ምክንያት መሆናቸውም ነው የተገለጸው፡፡

ክለቡ በአርሰናል ከተሸነፈ በኋላ መልበሻ ክፍል ውስጥ አለመግባባቶች ተፈጥረው እንደነበር የተዘገበ ሲሆን ፥በተለይም ክለቡ ከፍተኛ የዝውውር የከፈለባቸው ተጫዋቾች ጥሩ አቋም አለማሳየታቸው አለመግባባቱን እንዲፈጠር ምክንያት መሆናቸውም ነው የተገለጸው፡፡

በዚህም የማንቼስተር ዩናትድ ባለቤት የሆኑት የግሌዘር ቤተሰቦች ክለቡን ላለመሸጥ መወሰናቸው ተነግሯል።

ክለቡ በታሪኩ ዝቅተኛ የአክሲዮን ዋጋ ያስመዘገበው በፈረንጆቹ ግንቦት ወር 2020 ሲሆን ፥ በወቅቱ ክለቡ ከነበረው ዋጋ በ13 ነጥብ 5 በመቶ ዝቅ ብሎ እንደነበር ተዘግቧል፡፡

ይሁን እንጂ የክለቡ የአክሲዮን ዋጋ አሁን ላይ በ18 ነጥብ 5 በመቶ ዝቅ ያለ ሲሆን ፥ ይህም በክለቡ ታሪክ ከፍተኛው የአክሲዮን ዋጋ ቅናሽ ሆኖ መመዝገቡም ነው የተገለጸው፡፡

የግሌዘር ቤተሰቦች ዩናይትድን ለመሸጥ ለበርካታ ወራቶች ገዥ ቢያፈላልጉም እስካሁን ከቀረቡ ገዥዎች ጋር ስምምነት ላይ መድረስ አለመቻላቸውን ሲጂቲኤን ስፖርት አስነብቧል፡፡

የእንግሊዙ ባለሃብት ሰር ጂም ራትክሊፍ እና የኳታሩ ቢሊየነር ሼክ ጃሲም ቢን ሃማድ አል ታኒ ማንቼስተር ዩናይትድን ለመግዛት ጥያቄ ያቀረቡ ባለሀብቶች ሲሆን ፥ ያቀረቡት ገንዘብ በግሌዘር ቤተሰቦች ውድቅ ተደርጎባቸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.