Fana: At a Speed of Life!

የ2023ቱ የባሎንዶር ኮከብ ተጫዋቾች ዝርዝር ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2023ቱ የባሎንዶር ኮከብ ተጫዋቾች ዝርዝር ትላንት ምሽት ይፋ ተደርጓል፡፡

30 ተጫዋቾች በቀረቡበት የባሎዶር የኮከቦች ዕጩ ዝርዝር ውስጥ የአምስት ጊዜ አሸናፊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከፈረንጆቹ 2003 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ አለመካተቱ ተገልጿል፡፡

በአንጻሩ የዓለም ዋንጫ አሸናፊው ሊዮኔል ሜሲ እና በማንቼስተር ሲቲ ድንቅ ጊዜ እያሳለፈ የሚገኘው  ኤርሊንግ ብራውት ሃላንድ ለሽልማቱ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቷቸዋል፡፡

በሽልማቱ ዝርዝሩ ውስጥ ሶስት አፍሪካውያን ተጫዋቾች የተካተቱ ሲሆን÷ ግብጻዊው ሞሃመድ ሳላህ፣ናይጄሪያዊው አጥቂ ቪክቶሮ ኦሲሜን እንዲሁም ካሜሮናዊው ግብ ጠባቂ አንደሬ ኦናና ይገኙበታል፡፡

የባሎንዶር አሸናፊው በፈረንጆቹ ጥቅምት 30 በፓሪስ ቴአትር ዱቻ ቴሌት በሚደረገው ደማቅ ስነ ስርዓት የሚገለጽ መሆኑን ኢኤስፒኤን ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.