Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ሁለተኛ ዙር በኤሌክትሮኒክስ የተደገፈ የቤት ለቤት የኮቪድ-19 አሰሳ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ሁለተኛ ዙር በኤሌክትሮኒክስ የተደገፈ የቤት ለቤት የኮቪድ-19 አሰሳ ተጀምሯል።

የሁለተኛው በኤሌክትሮኒክስ የተደገፈ የቤት ለቤት የኮቪድ-19 አሰሳ በዋናነት ህብረተሰቡን ማስተማር እና የተገኙ መረጃዎችና ውጤቶች በፍጥነት በማስተላለፍ በሽታውን ለመከላከል የሚደረጉ ጥረቶችን ለማገዝ ከፍተኛ ሚና ሊጫወት እንደሚችል የጤና ሚንስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ የበሽታው ቁጥር መጨመር በጀመረበት በአሁኑ ወቅት የሚስተዋል መዘናጋትና ቸልተኝነት ሊታረም እንደሚገባም ጨምረው መግለፃቸውን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

በአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ዶክተር ሙሉጌታ እንዳለ በበኩላቸው፥ ሁለተኛው በኤሌክትሮኒክስ የተደገፈ የቤት ለቤት የኮቪድ-19 አሰሳ በመጀመሪያው መረሀግብር የተስተዋሉ ክፍተቶችን በመሸፈን አስፈላጊን ውጤት ማስመስገብ የሚያስችል ነው ብለዋል።

በመጀመሪያው የቤት ለቤት አሰሳ መረሀግብር 3 ነጥብ 1 ሚሊየን የሚሆኑትን የህብረተሰብ ክፍል ማዳረስ የተቸለ መሆኑን ዶክተር ሙሉጌታ ገልጸዋል።

በዚህም 971 ተጠርጣሪዎች የተለዩ ሲሆን፥ ከንአዚህም ውስጥ 21 ሰዎች ምልክት የታየባቸው እና 1 ሰው ደግሞ ቫይረሱ እንደተገኘበት ተነግሯል።

በመጀመሪያው ዙር በዜጎች ዘንድ ይቃደኛ ያለመሆን፣ ቤት ዘግቶ የመጥፋት እና መልክቶችን መጨመርን ጨምሮ ሌሎች ያለመተባበር ችግሮች እንደተስተዋሉ ተመልክቷል።

ህብረተሰቡም ለተጀመረው 5ኛው ዙር በኤሌክትሮኒክስ የተደገፈ የቤት ለቤት አሰሳ አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር ማድረግ እንዳለበትም ጥሪ አስተላልፈዋል።

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.