Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር የፊታችን ጥቅምት 17 ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የ2016 የውድድር ዘመን የፊታችን ጥቅምት 17 ቀን እንደሚጀመር ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡

ፌደሬሽኑ የ2016 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የሚጀምርበትን ቀን እና ሌሎች ተያያዥ መረጃዎችን ለተሳታፊ ክለቦች ማሳወቁ ተጠቁሟል፡፡

በዚህ መሰረትም የዕጣ ማውጣት መርሐ ግብሩ ጥቅምት 3 ቀን የሚካሄድ ሲሆን÷ ውድድሩ ደግሞ ጥቅምት 17 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚጀመር የፌዴሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

ክለቦች ምዝገባቸውን እስከ መስከረም 11 ቀን ድረስ እንዲሁም የሚጠበቅባቸውን የዳኞችና ታዛቢዎች ክፍያ እስከ መስከረም 30 ቀን እንዲያጠናቅቁም ፌዴሬሽኑ አሳስቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.