Fana: At a Speed of Life!

ማንቼስተር ሲቲና ሊቨርፑል  ድል ሲቀናቸው ማንቼስተር ዩናይትድ ተሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከሜዳቸው ውጪ የተጫወቱት ማንቼስተር ሲቲና ሊቨርፑል ድል ሲቀናቸው በሜዳው የተጫወተው ማንቼስተር ዩናይትድ ሽንፈት አስተናግዷል፡፡

ሊቨርፑል ወልቨርሃምፕተን ወንደረርስንን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ሲረታ÷ማንቼስተር ሲቲ ዌስትሃም ዩናይትድን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ከሜዳው ውጪ ሶስት ነጥብ ይዞ ተመልሷል፡፡

በሜዳው ብራይተን ሆቭ አልቢዮንን ያስተናገደው ማንቼስተር ዩናይትድ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

ሼፊልድ ዩናይትድን ያስተናገደው ቶተንሃም ሆትስፐር 2 ለ 1 አሽንፏል።

እንዲሁም ፉልሃም ሉቶን ታውንን አስተናግዶ 1 ለ 0 በማሸነፍ ሶስት ነጥብ ይዞ ወጥቷል።

ክሪስታን ፓላስን ያስተናገደው አስቶን ቪላ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.