Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በተሳተፈችበት የ ጄ ኬ ኤስ የካራቴ ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በተሳተፈችበት የ ጄ ኬ ኤስ (jks) የካራቴ ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች፡፡

በዱባይ እየተካሄደ ባለው የእስያ አፍሪካ ዋንጫ የjks የካራቴ ውድድር ላይ ተሳታፊ የሆኑት ሶስት ኢትዮጵያውያን ተወዳዳሪዎች ሜዳሊያ አግኝተዋል።

በመድረኩ በ60 ኪሎ ግራም የተወዳደረው ናትናኤል በየነ ለሀገሩ የወርቅ ሜዳሊያ ሲያስገኝ በተመሳሳይ ውድድር ኤፍሬም አደም በ84 ኪሎ ግራም እና አስቻለው ክብሩ የነሃስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆነዋል።

በውድድሩ ከ29 ሀገራት የተውጣጡ ስፖርተኞች እየተሳተፉበት ይገኛል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.