Fana: At a Speed of Life!

በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ሁለተኛ ዙር ቅድመ ማጣሪያ ባህር ዳር ከተማ ድል ቀናው

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 6 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ሁለተኛ ዙር ቅድመ ማጣሪያ ባህር ዳር ከተማ ድል ቀንቶታል።

ባህር ዳር ከተማ ከቱኒዚያው ክለብ አፍሪካን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2 ለ 0 አሸንፏል።

የድል ጎሎቹን ሀብታሙ ታደሰ ከእረፍት በፊት እና በጨዋታው መጠናቀቂያ ደቂቃዎች ላይ አስቆጥሯል።

የመልሱ ጨዋታ ከቀናት በኋላ የሚካሄድ ሲሆን፥ በደርሶ መልሱ ጨዋታ አሸናፊ የሚሆነው ቡድን በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተሳታፊ ይሆናል።

ባህር ዳር ከተማ በመጀመሪያው ዙር ቅድመ ማጣሪያ የታንዛኒያውን አዛም በደርሶ መልስ ጨዋታ ማሸነፉ ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.