Fana: At a Speed of Life!

የኮሮናቫይረስ ከዓለማችን ላይ እስከወዲያኛው ላይወገድ ይችላል- የዓለም ጤና ድርጅት

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኮሮናቫይረስ ከዓለማችን ላይ እስከወዲያኛው ላይወደገድ እንደሚችል የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።

የዓለም ጤና ድርጅት የድንገተኛ ህክምናዎች ዳይሬክተር ዶክተር ማይክ ረያን በትናንትናው እለት በሰጡት ማብራሪያ፥ ቫይረሱ የሚያበቃበትን ጊዜ መተንበይ ትክክል እይደለም ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ሁላችንም የኮሮናቫይረስ በዓለም ማህበረሰብ ዘንድ ሌላኛው ወረርሽኝ ሆኖ እስከወዲያኛው ሊቆይ ይችላል የሚለውን ከግምት ማስገባት አለብን ያሉት ዶክተር ረያን፥ ቫይረሱ እስከወዲያኛው አብሮን ሊኖርም ይችላል ብለዋል።

ኤች.አይ.ቪ ቫይረስ እስካሁን ከዓለማችን ላይ አልተወገደም፤ ሆኖም ግን የቫይረሱን ሁኔታ መረዳት እና መቆጣጠር ተችሏል ያሉት ዶክተር ረያን፥ “ማናችንም በሽታ የሚጠፋበትን ጊዜ መገመት እንችላለን የሚል እምነት የለኝም” ብለዋል።

አሁን ላይ ከ100 በላይ ክትባቶች ቀርበው ጥናት እየተደረገበት በሆኑን በመግለፅ፤ ለኮሮና ቫይረስ ክትባት ቢገኝኝ እንኳ የኮሮናቫይረስን የመከላከል ስራ ሰፊ ጥረቶችን የሚጠይቅ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይረከተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በበኩላቸው፥ አሁንም የሚደረጉ ጥረቶች ተጠናክረው ከቀጠሉ ቫይረሱን መቆጣጠር እንደሚቻል ገልፀዋል።

“እድሉ በእጃችን ላይ ነው፤ ይህ የሁሉም ሰው ጉዳይ ነው” ያሉት ዶክተር ቴድሮስ፥ “ይህንን ወረርሽኝ ለማስቆም ሁላችንም የበኩላችንን ማበርከት ይጠበቅብናል” ብለዋል።

በአሁኑ ሰዓት የኮሮናቫይረስ በዓለም ዙሪያ ከ4 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ ሰዎች ላይ የተገኘ ሲሆን፥ ከ297 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ህይወታቸው አልፏል።

በዓለም ዙሪያ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን በለዓይ ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ ማገገማቸው የጆንሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ያመለክታል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.