Fana: At a Speed of Life!

አርሰናል ከ6 ዓመታት በኋላ የመጀመሪያ የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታውን ዛሬ ምሽት ያደርጋል

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 9 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰሜን ለንደኑ ክለብ ከ6 ዓመታት ቆይታ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታውን ከኔዘርላንድሱ ፒኤስ ቪ ኢንድሆቭን ጋር ዛሬ ምሽት ያደርጋል፡፡

አርሰናል ለመጨረሻ ጊዜ በመድረኩ ተሳትፎ ያደረገው በፈረንጆቹ 2017 ሲሆን÷ በዚህም በጀርመኑ ክለብ ባየርሙኒክ ከምድብ ተሸንፎ መሰናበቱ የሚታወስ ነው፡፡

በማይክል አርቴታ ፊታውራሪነት የሚመሩት መድፈኞቹ ባለፈው ዓመት ባሳዩት ድንቅ እንቅስቃሴ የፕሪሚየር ሊጉ የዋንጫ ተፎካካሪ ከመሆናቸው ባለፈ የሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎን ማግኘት ችለዋል፡፡

ከጨዋታው በፊት ማይክል አርቴታ በሰጠው አስተያየት” ለሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ ስንል ተፋልመናል፣ጥረታችን ፍሬ አፍርቶ በከባዱ መድረክ መሳተፍ ችለናል” ብሏል፡፡

ምሽት 4 ሰዓት በሚደረገው ጨዋታም ደጋፊዎች ቡድኑን  እንዲያበረታቱ  ጥሪ አቅርቧል፡፡

ጋላታሳራይ ከኮፐን ሀገን፣ ባየር ሙኒክ ከማንቼስተር ዩናይትድ፣ ሲቪያ ከሌንስ፣ ሪያል ማድሪድ ከዩኒየን በርሊን፣ ስፖርቲንግ ብራጋ ከናፖሊ፣ ቤኔፊካ ከሳልዝ በርግ እና ሪያል ሶሽዳድ ከኢንተርሚላን ሌሎች ዛሬ ምሽት የሚደረጉ የሻምፒየንስ ሊግ መርሐ ግብሮች ናቸው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.