ድርቤ ወልተጂ በአንድ ማይል የሴቶች የጎዳና ላይ ሩጫ ሪከርድ ሰበረች
አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ድርቤ ወልተጂ በአንድ ማይል የሴቶች የጎዳና ላይ ሩጫ ሪከርድ በመስበር አሸነፈች፡፡
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሴቶች አንድ ማይል የሪጋ የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ ድል ቀንቷቸዋል፡፡
ርቀቱን አትሌት ድርቤ ወልተጂ በቀዳሚነት ስታጠናቅቅ ፍሬወይኒ ኃይሉ ደግሞ ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች፡፡
ድርቤ ወልተጂ በ4 ደቂቃ ከ21 ሰከንድ በሆነም ነው የዓለምን ሪከርድ የሰበረችው፡፡
ሁለተኛ የወጣችው ፍሬወይኒ ኃይሉ 4 ደቂቃ ከ23 ሰከንድ ከ6ሚሊ ሰከንድ በሆነ 2ኛ መውጣቷን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡