Fana: At a Speed of Life!

በቶሮንቶ ዋተርፍሮንት ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል

 

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 4 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በካናዳው የቶሮንቶ ዋተርፍሮንት ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል።

በሴቶች ውድድር ኢትዮጵያውያኑ ከ1 እስከ 4 ተከታትለው በመግባት አሸናፊ ሆነዋል።

ውድድሩን አትሌት ቡዜ ድሪባ 2 ሰአት ከ23 ደቂቃ ከ11 ሰከንድ በመግባት አሸናፊ ስትሆን ዋጋነሽ መካሻ በ1 ሰከንድ ልዩነት ሁለተኛ በመሆን አጠናቃለች።

አትሌት አፈራ ጎፋይ 2 ሰአት ከ23 ደቂቃ ከ15 ሰከንድ በመግባት የነሃስ ሜዳልያ ስታገኝ ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ፎዚያ ጀማል በ3 ሰከንድ ልዩነት አራተኛ በመሆን ውድድሯን ጨርሳለች።

በወንዶቹ ውድድር ኬንያዊው አትሌት ኤልቪስ ኪፕቾጌ 2 ሰአት ከ9 ደቂቃ ከ20 ሰከንድ በመግባት አሸናፊ ሲሆን፥ ኢትዮጵያዊው አትሌት አዱኛ ታከለ 2 ሰአት ከ10 ደቂቃ ከ26 ሰከንድ በመግባት በሁለተኛነት አጠናቋል።

ሌላኛው ኬንያዊው አትሌት አልፍሬድ ኪፕቸርቺር በሶስተኛነት ውድድሩን ጨርሷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.