Fana: At a Speed of Life!

ካቻ የተሰኘ የዲጂታል ፋይናንሲንግ ሰርቪስ አገልግሎቱን በይፋ አስጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ካቻ የተሰኘ የዲጂታል ፋይናንሲንግ ሰርቪስ የግል ክፍያ ሰነድ አውጪ በመሆን አገልግሎቱን በይፋ አስጀምሯል።
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ነው የተባለው አገልግሎቱ ከብሔራዊ ባንክ የአገልግሎት ፈቃድ ያገኘ እና የሞባይል የገንዘብ ዝውውርና ሌሎች የፋይናንስ አገልግሎቶችን በተለያየ ደረጃና አማራጮች ያካተተ መሆኑ ታውቋል።
አገልግሎቱ በአጭር ቁጥር፣ በአንድሮይድና አይ ኦ ኤስ መተግበሪያዎች በመጠቀም የሙከራ ትግበራውን ቀደም ሲል ሲያደርግ በመቆየት ስኬታማነቱን በማረጋገጥ ወደ ስራ መግባቱም ተመላክቷል።
በማስጀመሪያ ሥነ ስርዓቱ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ ዓሊ፥ እንደ ካቻ ዓይነት ባሉ የሚሰጡ አገልግሎቶች አካታች፣ በፈጠራ የተሞሉና ተዓማኒነት ያላቸው በመሆናቸው በሀገራዊ ፋይናንስ ውስጥ ማካተት የዲጂታል ኢትዮጵያን 2025 እውን ለማድረግ ሚናው የጎላ ነው ብለዋል።
መተግበሪያው የፋይናንስ አገልግሎት ለተጠቃሚዎች ምቹና ቀላል በሆነ አግባብ ያቀረበ መሆኑን በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ የተገኙ ተሳታፊዎች ገልፀዋል።
የካቻ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ተሾመ በየነ የካቻ ዓላማ ለደንበኞች በላቀ ቴክኖሎጂ የታገዘ ደህንነቱ የተጠበቀና የፋይናንስ አካታችነት ያለው የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት ማቅረብ ነው ብለዋል።
በሥነ ስርዓቱ ላይ በካቻና በተለያዩ ባንኮች፣ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማትና ሌሎች ስትራቴጂካዊ አጋሮች ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ፊርማ ተፈርሟል።
በታሪኩ ወልደሰንበት
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.