Fana: At a Speed of Life!

የዓለማችን ጥቁሩ ወንዝ ሩኪ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮንጎ ወንዝ ገባር የሆነው ሩኪ ወንዝ በዓለም እጅግ በጣም ጥቁሩ ወንዝ መሆኑን የዘርፉ ተመራማሪዎች አረጋግጠዋል፡፡

ተመራማሪዎች በአፍሪካ ወንዞች ላይ ባደረግነው ጥናት አግኝተነዋል ያሉት ይህ በኮንጎ የሚገኘው ወንዝ የዓለማችን ጥቁሩ ወንዝ የሚል ስያሜን ሰጥተውታል።

ወንዙ በአካባቢው ካለው ደን በተጠራቀመ ከፍተኛ መጠን ባለውና በካርበን ከበለጸጉ የተለያየ ቁሳቁስ፣ አትክልት፣ ባክቴሪያ እና አልጌ ብስባሽ ድብቅል ምክንያት መጥቆሩንም ነው ተመራማሪዎቹ የገለጹት።

ይህም የሆነው አካባቢው ደናማ ቦታ የሚወጣ የእጽዋት ብስባሽ የሚፈጠረው ውህድ በዝናብና በጎርፍ ታጥቦ ወደ ሩኪ ወንዝ ስለሚገባ ወንዙን ጥቁር ቀለም ገጽታ እንዳላበሰውም ይገልጻሉ፡፡

በዚህ ምክንያትም ወንዙ ጫፍ ላይ ቆሞ መልክን መመልከት እንደማይቻልና ጥቁረቱ ከአርጀንቲናው የሪዮ ኔግሮ ወንዝ የበለጠ መሆኑን የጥናቱ መሪ ዶክተር ትሬቪስ ድሬክ ይናገራሉ።

በአካባቢው ከሚገኘው ደን በዝናብ ታጥቦ ወደ ወንዙ የሚገባው ውህድ ብርሃንን ስለሚመጥ የወንዙ ጥቁረት ጎልቶ እንዲወጣ እንደሚያደርገው ይናገራሉ ተማራመሪው፡፡

የጥቁረቱ መጠን ሲገልጹም ” ልክ በአንድ የስኒ ሻይ ብዙ የሻይ ቅጠል ከረጢቶችን እንደመጨመር ነው” ይላሉ ፡፡

በስዊዘርላንድ የሚገኘው የኢ ቲ ኤች ዙሪክ የሳይንስ ተመራማሪዎች ቡድን በበኩላቸው÷ የወንዙ ውሃ በቀለም መለኪያ መሳሪያ ተለክቶ እንደተረጋገጠው የዓለም ጥቁር ውሃ ተብሎ ከሚታወቀው አማዞን ውስጥ ከሚገኘው ሪዮ ኔግሮ ወንዝ በ1 ነጥብ 5 እጥፍ እንደሚጠቁር አረጋግጠዋል፡፡

ምንም እንኳን ሩኪ ከኮንጎ ተፋሰስ 20 በመቶውን ብቻ የሚሸፍን ቢሆንም ባለው ከፍተኛ ካርበን ውህድ ምክንያት ከፍተኛ ደረጃን እንደሚይዝ ነው ተመራማሪዎች የሚናገሩት ፡፡

ሩኪ ከኮንጎ ወንዝ በአራት እጥፍ የካርበን ውህዶችን የሚይዝ እንደሆነ መረጋገጡን የኦዲቲ ሴንትራል ዘገባ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.