Fana: At a Speed of Life!

የ2023 የአፍሪካ እጩ ኮከብ ተጫዋቾች ዝርዝር ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የአፍሪካ እጩ ኮከብ ተጫዋቾችን ዝርዝር ይፋ አድርጓል፡፡

በምርጫ ዝርዝሩ ውስጥ 30 ተጫዋቾች በእጩነት የቀረቡ ሲሆን÷ 20 የሚሆኑት በአፍሪካ ክለቦች የሚጫወቱ ናቸው ተብሏል፡፡

በእጩ ዝርዝሩ ሞሃመድ ሳላህ፣ሪያድ ማህሬዝ፣አሺራፍ ሀኪሚ፣ሞሃመድ ኩዱስ፣ቪንሴንት አቡበከር፣ሳዲዮ ማኔ፣ቪክቶር ኦሲሜን እና ሲን ቦኖ የመሳሰሉ ከዋክብቶች ተካትተዋል፡፡

ከእጩ ኮከብ ተጫዋቾች ምርጫ በተጨማሪ የአፍሪካ የዓመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ፣ ምርጥ ወጣት ተጫዋች፣ምርጥ ብሄራዊ ቡድን ፣ ምርጥ ክለብ እና ምርጥ አሰልጣኝ እጩዎች ይፋ ሆነዋል፡፡

የኮከቦች ምርጫ የፊታችን ታሕሳስ 11 ቀን 2023 በሞሮኮ ማራካሽ ከተማ የሚደረግ መሆኑንም የካፍ መረጃ ያመላክታል፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.