Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ሀዋሳ ከተማና ቅዱስ ጊዮርጊስ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ5ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀዋሳ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡

ቀን 9 ሰዓት ላይ ሲዳማ ቡናን የገጠመው ሀዋሳ ከተማ በእዮብ አለማየሁ ብቸኛ ግብ 1 ለ 0 በማሸነፍ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አሳክቷል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ሀዋሳ በ9 ነጥቦች 6ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ÷ተሸናፊው ሲዳማ ቡና  ደግሞ በ5 ጨዋታዎች 4 ነጥቦችን በመሰብሰብ 11ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

ምሽት 12 ሰዓት ላይ በተካሄደው ሌላኛው መርሐ ግብር የሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ  ኢትዮጵያ መድህንን 3 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት በማሸነፍ የሊጉን መሪነት አጠናክሯል፡፡

የፈረሰኞቹን የማሸነፊያ ግቦች አቤል ያለው በፍፁም ቅጣት ምት፣ ሞሰስ አዶ እና አማኑኤል ኤርቦ ደግሞ በጨዋታ አስቆጥረዋል፡፡

ውጤቱን ተክትሎም ቅዱስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥቡን 13 በማድረስ የሊጉን መሪነት ሲያጠናክር ÷ኢትዮጵያ መድን 5 ነጥቦችን በመያዝ 10ኛ ደረጃ ተቀምጧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.