Fana: At a Speed of Life!

የማይክል ጃክሰን ጃኬት በጨረታ 306 ሺህ ዶላር ተሸጠ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ14 ዓመታት በፊት ሕይወቱ ያለፈው አሜሪካዊው የፖፕ ሙዚቃ ንጉሥ ማይክል ጃክሰን ጃኬት ለጨረታ ቀርቦ 306 ሺህ ዶላር መሸጡ ተሰምቷል፡፡

ጃኬቱ በ1980ዎቹ ማይክል ጃክሰን ፔፕሲ ኮላን ሲያስተዋውቅ ለብሶት እንደነበር ተገልጿል፡፡

ቀደም ሲልም “ሙን ዎክ ዳንስ” የተባለውን የእግር ዳንስ በፓሪስ ባሳየበት ወቅት የለበሰው ኮፍያ ለጨረታ ቀርቦ 67 ሺህ ዶላር መሸጡን አስታውሶ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በሌላ በኩል የማይክል ጃኬት ለጨረታ በቀረበበት መድረክ የቀድሞዋ እንግሊዛዊት አቀንቃኝ ኤሚ ወይንሃውስ የፀጉር ጌጥ በ22 ሺህ 900 ዶላር ተሽጧል፡፡

የፀጉር ጌጡ በመጨረሻ አልበሟ “ደኅና አይደለሁም” (I’m not good) በተሰኘው የሙዚቃ ቪዲዮዋ ላይ የተጠቀመችው መሆኑም ተመላክቷል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.