Fana: At a Speed of Life!

በቤይሩት ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል

 

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በቤይሩት ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታዎች በተደረገው ውድድር የቦታውን ሪከርድ በመስበር አሸነፉ፡፡

በቤይሩት ማራቶን በወንዶች ጋዲሳ ጣፋ 02፡10፡34 በመግባት የቦታውን ሪከርድ በማሻሻል በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ ጎጃም በላይነህ ደግሞ ሁለተኛ ደረጃ ይዞ አጠናቋል፡፡

እንዲሁም በሴቶች በተደረገው የማራቶን ውድድር ሙሉጎጃም ብርሃን 02፡19፡32 በመግባትና የቦታውን ሪከርድ በማሻሻል በአንደኝነት ስታጠናቅቅ ጌጤ ዱከሌ እና አስመሬ በየነ ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ ይዘው በተከታታይ በመግባት ውድድሩን አጠናቀዋል፡፡

በቤይሩት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ቆንሱል ጀነራል አምባሳደር ተመስገን ዑመር በቦታው በመገኘት ኢትዮጵያውያን አትሌቶችን ያበረታቱ ሲሆን÷ በውድድሩ አዘጋጆች የተዘጋጀውን ሽልማት ለአሸናፊዎች ማበርከታቸውን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.