የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ2016 የውድድር ዘመን የመጀመሪያ ዙር መርሐ ግብር ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የእግር ኳስ ፌደሬሽን የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ2016 የውድድር ዘመን የመጀመሪያ ዙር መርሐ ግብርን ይፋ አድርጓል፡፡
በዚህ መሰረትም ፕሪሚየር ሊጉ ሀዋሳ ከተማ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ህዳር 16 ቀን 2016 ዓ.ም በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በሚያደርጉት ጨዋታ ይጀመራል፡፡
በዕለቱም ልደታ ክፍለ ከተማ ከአርባ ምንጭ ከተማ እንዲሁም አዲስ አበባ ከተማ ከሲዳማ ቡና ጨዋታቸውን የሚያከናውኑ ይሆናል፡፡
ሙሉ የጨዋታ መርሐ ግብሩ እንደሚከተለው ቀርቧል፡-