Fana: At a Speed of Life!

በዲጂታል የነዳጅ ግብይት ሥርዓት 124 ቢሊየን ብር ግብይት መፈጸሙ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዲጂታል ግብይት ሥርዓት ተግባራዊ ከተደረገ ጀምሮ 124 ቢሊየን ብር የሚገመት ግብይት መፈጸሙን የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን አስታወቀ።

የባለሥልጣኑ የነዳጅ ውጤቶች ግብይት ስታንዳርድ ጥናትና ምርምር ዳይሬክተር ለሜሳ ቱሉ እንደገለጹት÷ የነዳጅ ግብይት በዲጂታል መካሄዱ ብዙ ጥቅሞች አስገኝቷል።

በተለይም በዘርፉ ያለውን ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር፣ የነዳጅ ብክነትን በማስቀረትና የነዳጅ ግብይት ሥርዓቱንም ቀልጣፋ በማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽዖ አበርክቷል ነው ያሉት።

ይህንንም ተከትሎ የዲጂታል የነዳጅ ግብይት በዲጂታል ሥርዓት መካሄድ ከጀመረ አንስቶ እስካሁን 124 ቢሊየን ብር የሚገመት ግብይት እንደተፈጸመ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በቅርቡ በወረቀትና በሰው ንክኪ የሚፈጸም የነዳጅ ኩፖን ሽያጭ አገልግሎት አሠራርን በዲጂታል ኩፖን ለመቀየር በሂደት ላይ መሆኑን ጠቁመዋል።

ጎን ለጎንም የድጎማ ሥርዓቱን ያላግባብ የሚጠቀሙ ተሽከርካሪዎችና የነዳጅ ማደያዎችን በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ እየተሰራ መሆኑንም ገልፀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.