Fana: At a Speed of Life!

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በቫሌንሺያ ማራቶን እንደሚሳተፍ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በፈረንጆቹ ታሕሳስ 3 ቀን በሚካሄደው የቫሌንሺያ ማራቶን እንደሚሳተፍ አስታወቀ፡፡

አትሌቱ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባሰፈረው ጽሑፍ÷ ከብዙ ጊዜ ጉዳት በኋላ በቫሌንሺያ ማራቶን እንደሚሳተፍ አስታውቋል።

ወደ ሩጫ ለመመለስ ከባድ የልምምድ ጊዜዎችን ማሳለፉን የገለፀው አንጋፋው አትሌት÷ “በፈረንጆቹ ታህሳስ 3 ቀን በሚካሄደው የቫሌንሺያ ማራቶን አቅሜን እፈትሻለሁ” ብሏል።

የቫሌንሺያ ማራቶን አዲስ ጅማሮዬ ነው ያለው አትሌቱ ÷ወደ ውድድር እንዲመለስ ድጋፍ ላደረጉለት አድናቂዎቹ ና የስፖርት ቤተሰቡ ምስጋና አቅርቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.