Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወልቂጤ ከተማን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናከረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 24ኛ ሳምንት የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወልቂጤ ከተማን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናከረ።

ምሽት 12:00 ሰዓት ላይ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወልቂጤ ከተማን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሱሌማን ሀሚድ እና ፉዓድ ፈረጃ ሲያስቆጥሩ፤ የወልቂጤ ከተማን ብቸኛ ጎል ሳምሶን ጥላሁን አስቆጥሯል።

ውጤቱን ተከትሎ የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነጥቡን 50 በማድረስ መሪነቱን አጠናክሯል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.