Fana: At a Speed of Life!

ቪክተር ኦሲሜን የአፍሪካ ኮኮብ ተጫዋች ሆኖ ተመረጠ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢሲ) ናይጄሪያዊዉ የናፖሊ አጥቂ ቪክተር ኦሲሜን የ2023 የአፍሪካ ኮከብ ተጫዋች ሽልማትን አሸንፏል።

በጣሊያን ሴሪ አ የ2022/23 የውድድር ዘመን ኦሲሜን የስኩዴቶው ሻምፒዮን ከሆነው ናፖሊ ጋር ምርጥ ጊዜን ያሳለፈ ሲሆን፥ 26 ጎሎችን በማስቆጠር የሴሪ ኤው ኮከብ ጎል አግቢ እንደነበር አይዘነጋም።

በሌላ በኩል ሞሮኳዊው በረኛ ያሲን ቦኖ የዓመቱ ምርጥ በረኛ ሽልማትን፤ የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዋሊድ ረግራጊ ደግሞ የምርጥ አሰልጣኝ ሽልማትን አሸንፈዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.