Fana: At a Speed of Life!

የብራዚል ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮ-ብራዚል የንግድ እና ኢንቨስትመንት ፎረም በአዲስ አበባ በተለያዩ ሁነቶች ተካሂዷል።

የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ÷ የብራዚል ባለሃብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮች እና በድሬደዋ ነፃ ንግድ ቀጠና ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ኮርፖሬሽኑ በተለይም ለውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት በሰጠው ልዩ ትኩረት የአሠራር ሪፎርሞችን ተግባራዊ በማድረግ እና ባጠረ ቢሮክራሲ በዘመናዊ መንገድ አገልግሎት በመስጠት ኢንቨስተሮችን እያስተናገደ እንደሚገኝ አሳውቀዋል።

በቅርቡ ኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀሏ ከብራዚል ጋር ያላትን የቀደመ ግንኙነት ይበልጥ በኢንቨስትመንት በማሳደግ በኩል የሚኖረው ሚና ጉልህ እንደሆነ መናገራቸውን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

ለዚህም የብራዚል አምራች ኩባንያዎች እና ባለሃብቶች በተለይም በማኑፋክቸሪንግ እና በአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ በኢንዱስትሪ ፓርኮች እና በድሬደዋ ነፃ ንግድ ቀጠና እንዲሰማሩ ጠይቀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.