Fana: At a Speed of Life!

ቅዱስ ጊዮርጊስ ሀዋሳ ከተማን 3 ለ 0 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በስምንተኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሀዋሳ ከተማን 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡

ቀን 9 ሰዓት በተደረገው ጨዋታ አቤል ያለው የቅዱስ ጊዮርጊስን ሶስት የድል ጎሎች ከእረፍት በፊት በማስቆጠር ሃትሪክ ሰርቷል፡፡

በዚህም አቤል ያለው በ2016ቱ የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ከባህርዳር ከተማው አጥቂ ሀብታሙ ታደሰ በመቀጠል ሃትሪክ መስራት የቻለ ሁለተኛው ተጫዋች ሆኗል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ተስተካካይ አንድ ጨዋታ እየቀረው በ16 ነጥብ ለጊዜው ሁለተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ሀዋሳ ከተማ በአንፃሩ በ9 ነጥቦች በነበረበት 8ኛ ደረጃ ላይ ለመቆየት ተገዷል፡፡

እንዲሁም በፕሪሚየር ሊጉ 8ኛ ሳምንት ምሽት 12 ሰዓት ላይ በተካሄደ ጨዋታ መቻል ወልቂጤ ከተማን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የመቻል የማሸነፊያ ግቦችን ከነዓን ማርክነህ እና ቺጂኦኪ ናሞዲ አስቆጥረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.