Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የላዳ ተሽከርካሪዎችን ለመገጣጠምና ለማምረት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያው ተሽከርካሪ አምራች ኩባንያ ላዳ እና ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ተሽከርካሪዎችን በኢትዮጵያ ለማምረት እና ለመገጣጠም የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱን የፈረሙት የኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አምባሳደር ሱሌማን ደደፎ  እና የላዳ የወጪ ንግድ ዳይሬክተር፣ የሽያጭ እና ማርኬቲንግ ምክትል ፕሬዚዳንት ኢሊያ ሳቪኖቭ ናቸው፡፡

አምባሳደር ሱሌማን በፊርማ ሥነ- ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የሩሲያ ባለሐብቶች በተለይም በማዕድን፣ በግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ እና በቴክኖሎጂ ዘርፎች መዋዕለ-ነዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ለዚህም መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡

ዛሬ በተፈረመው ስምምነት መሰረትም÷ ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የላዳን ያልተጠናቀቁ ምርቶች በመገጣጠም ሥራ የሚጀምር ይሆናል ብለዋል፡፡

በቀጣይም ግብዓቶችን በማስመጣት ተሽከርካሪዎችን ለገበያ እንደሚያቀርብም ነው ያስታወቁት፡፡

ኢሊያ ሳቪኖቭ በበኩላቸው÷ በርካታ የሩሲያ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ መዋዕለ-ነዋያቸውን ለማፍሰስ ፍላጎት እያሳዩ መሆኑን  ተናግረዋል፡፡

የሩሲያ ኢትዮጵያ የቢዝነስ ፎረምም ከነገ በስቲያ እንደሚካሄድ ጠቁመው÷ ይህም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የኢንቨስትመንት ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚያግዝ አመላከትዋል፡፡

በወንደሰን አረጋኸኝ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.