Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል ከ200 ሚሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት አምስት ወራት ከ200 ሚሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ 43 ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መውሰዳቸውን የጋምቤላ ክልል ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ።

የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ሎው ኡቡፕ (ዶ/ር) እንደገለጹት÷ የኢንቨስትመንት ፈቃዱ የተሰጠው በግብርና፣ በኢንዱስትሪና በአገልግሎት ዘርፎች ነው፡፡

በእነዚህ ፈቃድ በተሰጠባቸው ዘርፎች ለማሰማራት ወደ ክልሉ የሚገቡ ባለሃብቶች ፍሰት እየጨመረ መምጣቱንም ነው ለኢዜአ የተናገሩት፡፡

ፈቃድ የወሰዱት ባለሃብቶች ሙሉ ለሙሉ ወደ ሥራ ሲገቡ ከ2 ሺህ 500 ለሚበልጡ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥሩ አስታውቀዋል፡፡

በክልሉ የኢቨስትመንት አማጮችን ምቹ ከማድረግ በተጨማሪ በምርት ማሳደጊያ፣ በግብዓት አቅርቦትና በገበያ ትስስር ረገድም የኮሚሽኑ ድጋፍና ትብብር ሊጠናከር እንደሚገባ ባለሃብቶቹ ጠይቀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.