Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ለተከሰቱ የተፈጥሮ አደጋዎች መንግሥት 11 ቢሊየን ብር መድቦ እየሠራ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ለተከሰቱ የተፈጥሮ አደጋዎች መንግሥት 11 ቢሊየን ብር ወጭ በማድረግ የረድዔት ሥራዎችን እየሠራ መሆኑን የአደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት÷ ድርቁ ወደ ረሃብ ተቀይሯል የሚሉ መረጃዎች ሌላ ዓላማ ይዘው የሚንቀሳቀሱ አካላት የሚያዘዋውሯቸው እንጂ ሣይንሳዊና እውነተኛ መሠረት የላቸውም፡፡

እንዲህ ያለ መረጃ በማሠራጨት ላይ ያሉ ወገኖች ከድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

ድርቁ ከተከሰተ በኋላ መንግሥት የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰው÷ አጋር ተራድዖ ድርጅቶች ያደረጉትን ከ4 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ድጋፍ ጨምሮ በአጠቃላይ ለሰብዓዊነት የሚውል የ15 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ድጋፍ መገኘቱንም ነው ያስረዱት፡፡

ድርቁ በአማራ ክልል ባሉ ሥምንት ዞኖች፣ በአፋር ክልል ባሉ ሦስት ዞኖችና በትግራይ ክልል በሚገኙ ሦስት ዞኖች መከሰቱን ጠቁመው፤ ተጎጂዎችን ለመድረስ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አብራርተዋል።

ኮሚሽነሩ በአንዳንድ አካባቢዎች ሰብዓዊ ዕርዳታ ለማድረስ አሁንም የፀጥታ ችግሮች ፈተና መሆኑን አመልክተዋል።

በአፈወርቅ እያዩ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.