Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ባለፉት ሶስት ወራት 880 ሺህ ኩንታል ሰሊጥ ለገበያ መቅረቡ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ሶስት ወራት 880 ሺህ ኩንታል የሰሊጥ ምርት ለገበያ መቅረቡን የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አስታውቋል፡፡

የቢሮው ሃላፊ ኢብራሂም መሃመድ (ዶ/ር) እንዳሉት÷ በክልሉ ከሚመረቱ የቅባት እህሎች ግንባር ቀደሙ እና ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬን የሚያስገኘው የሰሊጥ ምርት ነው፡፡

ሰሊጥ በክልሉ ባለፉት አራት ዓመታት ውስጥ የምርት መጠን መቀነስ በማሳየቱ አምራቹን ስጋት ውስጥ ከትቶ እንደነበር አንስተዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ ወራት ላይ 880 ሺህ ኩንታል የሰሊጥ ምርት ለገበያ መቅረቡን ጠቁመው÷ ይህም በቀጣይ የሚገኘው የምርት መጠን እንደሚጨምር አመላካች ነው ብለዋል፡፡

በሌሎች የቅባት እህል ምርቶች የምርት መጠን መሻሻል እየታየ እና የግብይት ስርዓቱ ላይ ለውጥ ማምጣት መቻሉም ተጠቁሟል፡፡

በስንታየሁ አራጌ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.