Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ባንክ ኢትዮጵያን ጨምሮ 6 የአፍሪካ ሀገራት ከፍተኛ የኢኮኖሚ ዕድገት እንደሚያሳዩ ተነበየ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንጆቹ 2024 ኢትዮጵያን ጨምሮ ሥድስት የአፍሪካ ሀገራት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ዕድገት እንደሚያሳዩ የዓለም ባንክ በሪፖርቱ ጠቁሟል፡፡

የዓለም ባንክ በዚህ ሣምንት ይፋ ባደረገው የዓለም ኢኮኖሚ ትንበያ ኒጀር፣ ሴኔጋል እና ሩዋንዳ በፈረንጆቹ 2024 ከዓለም ከፍተኛ የኢኮኖሚ እድገት ከሚያስመዘገቡ ሀገራት መካከል እንደሚሆኑ አመላክቷል።

በመጀመሪያ ደረጃ የተቀመጠችው ኒጀር በዓመቱ የ12 ነጥብ 5 በመቶ እድገት እንደምታሳይ ነው ያስታወቀው፡፡

ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ኮትዲቯር እና ኢትዮጵያም ሌሎች በዚህ የፈረንጆች ዓመት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የኢኮኖሚ እድገት ያሳያሉ ተብለው የሚጠበቁ እንደሆኑ የዓለም ባንክ በሪፖርቱ አንስቷል፡፡

በዚህ ዓመት ከሰሀራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራት በአማካይ አምስት በመቶ እድገት እንደሚኖራቸው ነው የተጠቆመው፡፡

ሆኖም ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ እድገት በፈረንጆቹ 2023 ከነበረበት 3 ነጥብ 7 በመቶ እና 4 ነጥብ 4 በመቶ ወደ 2 ነጥብ 9 በመቶ ዝቅ ማለቱ ተነግሯል።

ለዚህ ምክንያት ተብሎ የሚነሳው የተለያዩ የሀገር ውስጥ ፖሊሲ ርምጃዎች እና መሰል ችግሮች እንደሆኑ የዓለም ባንክ አስታውቋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.