Fana: At a Speed of Life!

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ናኦሚ ግርማ የአሜሪካ የ2023 የምርጥ ተጫዋች ሽልማትን አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሳን ዲያጎ ዌቭ የሴቶች ቡድን እየተጫወተች የምትገኘው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ናኦሚ ግርማ የአሜሪካ የ2023 የሴቶች ምርጥ ተጫዋች ሽልማትን አሸንፋለች፡፡

በዚህም የ23 አመቷ ናኦሚ በአሜሪካ ሴቶች እግርኳስ ታሪክ የመጀመሪያዋ ተከላካይ እና ሁለተኛዋ ጥቁር የአመቱ ምርጥ ሴት ተጫዋች ሽልማት አሸናፊ መሆን ችላለች፡፡

ናኦሚ የአሜሪካ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በ2023 ባደረጋቸው 16 የፊፋ የሴቶች የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ላይ የቡድኑን የተከላካይ ክፍል በብቃት መምራቷ ተገልጿል፡፡

ከሽልማቱ በኋላ ናኦሚ “ሽልማቱን በማሸነፌ ደስ ብሎኛል፤ከዚህ ሽልማት ጀርባ ሌሎች የቡድን አጋሮቼ ቁልፍ ሚና ነበራቸው፤ያለፈው ዓመት ለእኔ እና ለብሄራዊ ቡድኑ ታሪካዊ ዓመት ነበር” ብላለች፡፡

የምርጥ ተጫዋች ምርጫው ከአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኞች፣ ተጫዋቾች፣ ከእግር ኳስ ዳይሬክተሮች የቦርድ አባላት፣ ከብሄራዊ የሴቶች እግር ኳስ ሊግ ዋና አሰልጣኞች፣ ከሚዲያ አባላት እና ከአስተዳዳሪዎች በተሰጠ ድምፅ የተወሰነ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ናኦሚ ከፈረንጆቹ 2021 ጀምሮ በአሜሪካ ብሄራዊ ቡድን የተካላከይ ስፍራ ላይ እየተጫወተች ትገኛለች፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.