Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ባህርዳር ከነማ 4ኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ14ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚርሊግ ባህርዳር ከተማ 4ኛ ተከታታይ ሽንፈቱን አስተናግዷል፡፡

ቀን 9 ሰዓት ላይ ሀድያ ሆሳዕናን የገጠመው የአሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው ቡድን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተሳታፊ የነበረው ባህርዳር ከተማ የውጤት ቀውስ ውስጥ ገብቷል፡፡

የቡድኑ አሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው በ5ኛው ደቂቃ ጎል መቆጠሩ ተጫዎቾቻቸው ጫና ውስጥ እንዲገቡ በማድረጉ መሸነፋቸውን ከጨዋታው በኋላ ተናግረዋል፡፡

የባሕር ዳር ከነማን የውጤት ቀውስ አስመልክቶ ከዕለቱ ጨዋታ በፊት የክለቡ የቦርድ አባላት ከተጫዋቾች እና የአሰልጣኝ ቡድን አባላት ጋር ተወያይተው እንደነበር ክለቡ አስታውቋል፡፡

በውድድር ዓመቱ የዋንጫ ተፎካካሪነት ግምት ተሰጥቷቸው የነበሩት የጣና ሞገዶቹ በ14 ጨዋታዎች 19 ነጥቦችን ብቻ በመያዝ 8ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 14ኛ ሳምንት ጨዋታዎች መካሄዳቸውን ሲቀጥሉ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ሀዋሳ ከተማና ሀምበሪቾ ዱራሜ ይጫወታሉ፡፡

በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓ በተካሄደ ሌላ ጨዋታ ሀዋሳ ከተማ ሀምበሪቾ ዱራሜን 2 ለ 0 አሸፏል፡፡

የሀዋሳ ከተማን ሁለት ጎሎች አሊ ሱሌማን እና ተባረክ ሄፋሞ አስቆጥረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.