Fana: At a Speed of Life!

የኮትዲቯር ብሔራዊ ቡድን በፕሬዚዳንት አላሳን ኦታራ እውቅናና ሽልማት ተበረከተለት

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮኑ የኮትዲቯር ብሔራዊ ቡድን በሀገሪቱ ፕሬዚዳንት አላሳን ኦታራ እውቅናና ሽልማት ተብርክቶለታል፡፡

ዝሆኖቹ ካለፈው ማክሰኞ ጀምሮ በአቢጃን ጎዳናዎች ላይ የአፍሪካን ዋንጫ በመያዝ ለብሔራዊ ቡድኑ ደጋፊዎች እና ለሀገሪቱ  ዜጎች የክብር ዋንጫውን በተለያዩ የትርዒት ሰልፎች አሳይተዋል፡፡

ከሻምፒዮኖቹ የትርዒት ሰልፍ መጠናቀቅ በኋላም  ትላንት ምሽት ፕሬዚዳንት አላሳን ኦታራ ለብሔራዊ ቡድኑ የክብር ሜዳሊያ እና የገንዘብ ሽልማት አብርክተዋል፡፡

በተጨማሪም ብሔራዊ ቡድኑ የሀገሪቱ ብሄራዊ የክብር ሽልማት የተሰጠው ሲሆን÷ የቡድን ሃላፊዎችም የኮማንደርነት ማዕረግ አግኝተዋል፡፡

በተጨማሪም አሰልጣኙ እና የቡድኑ ተጫዋቾች “ቻቫሊየር” የተሰኘ ከፍተኛ የክብር ሽልማት ማዕረግ ተበርክቶላቸዋል፡፡

ኮትዲቯር በአፍሪካ ዋንጫ ከምድብ ሁለት ጊዜ ተሸንፋ በምርጥ ሶሰተኛነት ጥሎ ማለፉን የተቀላቀለች ሲሆን÷ ሴኔጋልን በመለያ ምት፣ ማሊን  እና ዴሞክራቲክ ኮንጎን ደግሞ በጨዋታ በመርታት  ነው ለፍጻሜ የደረሰቸው፡፡

ኮትዲቯር በፍጻሜው በናይጄሪያ በመጀመሪያ አጋማሽ ስትመራ ብትቆይም ተጫዋቾች ባደረጉት ተጋድሎ በፍራንክ ኬሲ እና ሰባስቲያን ሃለር ሁለት ግቦች የአፍሪካን ዋንጫ ማንሳት ችላለች፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.