Fana: At a Speed of Life!

ዮሴፍ ገብረወልድ የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆኖ ተሾመ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አሰልጣኝ ዮሴፍ ገብረወልድ የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆኖ ተሾሟል፡፡

ቡድኑ በጋና አስተናጋጅነት በሚካሄው የአፍሪካ ጨዋታዎች ውድድር ላይ ተሳታፊ መሆኑ ይታወቃል።

ለዚህም ከየካቲት 29 ቀን ጀምሮ ለሚካሄው ውድድርም ቡድኑን እንዲያዘጋጅ አሰልጣኝ ዮሴፍ ገብረወልድ መሾሙን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

አሰልጣኝ ዮሴፍ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ የሆነውን የአርባምንጭ ከተማ የሴቶች ቡድንን በማሰልጠን ላይ ነበር፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.