Fana: At a Speed of Life!

“ለአፍሪካ ለውጥ ዲጂታላይዜሽንን መታጠቅ” በሚል ርዕስ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ጎን ለጎን “ለአፍሪካ ለውጥ ዲጂታላይዜሽንን መታጠቅ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ የፓናል ውይይት በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ነው፡፡

በፓናል ውይይቱ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ተወካዮች እና የዓለም አቀፍ ተቋማት አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ በዚህ ወቅት እንዳሉት ፥ ለአፍሪካ ዘላቂና አካታች እድገት የዲጂታላዜሽን አጀንዳ ወሳኝነት አለው።

ዲጂታላይዜሽን በመጠቀም እየደረሰ ያለውን የአየር ንብረት ለውጥን መከላከል ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡

ኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚን ለመጠቀም “ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025” በሚል ማዕቀፍ እየሰራች እንደምትገኝ ጠቅሰው÷ በቴሌኮም፣ ዲጂታል ፋይናንስ፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስና ኢንተርኔት ተደራሽነት ላይ እየሰራች ነው ብለዋል፡፡

ዲጂታላይዜሽን ኢንቨስትመንትን ለማቀላጠፍ ጉልህ ሚና እንዳለው በማንሳትም አፍሪካውያን በዘርፉ በትኩረት መስራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡

በፓናል ውይይቱ ላይ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ፣ የደብሊውኢኤፍ የአፍሪካ እና የዓለም ዓቀፍ ሪጅናል አክሽን ግሩፕ መስራች ላንድሬይ ሰኚ(ፕ/ር)፣ የቤኒኑ የአፍሪካ ትልቁ የሞባይል ዋሌት ኩባንያ ኦናፍሪክ መስራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚ ዳሬ ኦኮዱጁ እና የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከፍተኛ አማካሪና የቴክ ቶክ ቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ሰሎሞን ካሳ ሃሳባቸውን አጋርተዋል።

በምስክር ስናፍቅ

#Ethiopia #Africa

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting/
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.