የአፍሪካን እምቅ ሃብት መጠቀም በአባል ሀገራቱ መካከል የዳበረ ትብብርና የወንድማማችነት እሴት ይፈልጋል – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ አህጉርን እምቅ ሃብት መጠቀም በአባል ሀገራቱ መካከል የዳበረ ትብብር እና የወንድማማችነት እሴት ይፈልጋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ፥ ከቡሩንዲ፣ አንጎላ፣ ሞዛምቢክ እና ናይጄሪያ ፕሬዚዳንቶች ጋር የጋራ የልማት ጥረቶችን የተመለከቱ የሁለትዮሽ ውይይቶች ማካሄዳቸውን ገልጸዋል፡፡
“የአህጉራችንን እምቅ ሃብት መጠቀም በአባል ሀገራት መካከል የዳበረ ትብብር እና የወንድማማችነት እሴት ይፈልጋል” ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡