Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ አርሰናል እና ሊቨርፑል ድል ቀናቸው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል እና ሊቨርፑል ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡

ሊቨርፑል ከብሬንትፎርድ ጋር ባደረገው ጨዋታ 4 ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የሊጉን መሪነት አጠናክሯል፡፡

በሌላ በኩል አርሰናል በርንሌይን 5 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት ሲያሸንፍ÷ወልቭስ ደግሞ ቶተንሃምን 2 ለ1 አሸንፏል፡፡

በተመሳሳይ አስቶንቪላ ፉልሃምን 2 ለ 1 ሲረታ÷ ኖቲንግሃም ፎረስት ዌስት ሃምን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡

ኒውካስል እና በርንማውዝ ባደረጉት ጨዋታ ደግሞ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.