Fana: At a Speed of Life!

ለከፍተኛ የደም ግፊት ተጋላጮች እነማን ናቸው?

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከፍተኛ የደም ግፊት መኖር ለአጣዳፊ የልብ ውጋት ወይም በደም ዝውውር ማነስ ምክንያት ለሚከሰት የአዕምሮ ስራ መታወክ (ስትሮክ) የመጋለጥ ዕድልን ይጨምራል፡፡

ለመሆኑ ለከፍተኛ የደም ግፊት ተጋላጭ የሚሆኑት ምን አይነት ሰዎች ናቸው?

ለከፍተኛ የደም ግፊት ተጋላጭ ከሚሆኑ ሰዎች ውስጥ ዕድሜያቸው ከ30 ዓመት በላይ የሆኑ፣ በተለይም ከ45 ዓመት በላይ የሆኑ፣ የሰውነት ክብደታቸው ከፍተኛ የሆነ፣ የኩላሊት በሽታ ያለባቸው፣ የስኳር በሽታ ያለባቸው እና የደም ግፊት በሽታ በቤተሰባቸው ታሪክ ያለባቸው (በበሽታው የተጠቃ የቅርብ ዘመድ ካለ) ሰዎች ይገኙበታል።

እንዲሁም ብዙ ጊዜ የሚጨነቁ፣ የሰውነት እንቅስቃሴ የማያዘወትሩ፣ ሲጋራ የሚያጨሱ ወይም አደንዛዥ እጽ የሚጠቀሙ፣ የአልኮል መጠጥ የሚያዘወትሩ፣ ብዙ ጊዜ ጨው የበዛበት ምግብ የሚመገቡ እና በቂ ፍራፍሬና አትክልት የማይመገቡ ሰዎች ለከፍተኛ የደም ግፊት ተጋላጭ ናቸው፡፡

ከፍተኛ የደም ግፊት ሲኖር የህመም ስሜት ወይም ሌሎች ምልክቶች ላይታዩ/ላይኖሩ እንደሚችሉ ከአዲስ አበባ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በዚህ የደም ግፊትዎን መጠን ማወቅ ሕይወትዎን ሊያድን ይችላልና የደም ግፊትዎን በየጊዜው መለካት ይመከራል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.