Fana: At a Speed of Life!

ከ40 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት 40 ሚሊየን 125 ሺህ ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የገቢ ኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ።

በሶማሊ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እና በጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተደረገ የመረጃ ቅብብሎሽ እና የክትትል ሥራ የካቲት 26 ቀን 2016 ዓ.ም አዳዲስ ስማርት የሞባይል ስልኮች መያዛቸው ተገልጿል።

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ ምንም አይነት የጉምሩክ ስነ-ስርዓት ሳይፈፀምባቸው ወደ ሀገር ውስጥ በመጓጓዝ ላይ እያሉ ልዩ ቦታው ጨረቴ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አባላት እና በጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በቁጥጥር ስር ሊውል መቻሉን የገቢዎች ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.