Fana: At a Speed of Life!

ዓየር መንገዱ ሙሉ በሙሉ በሴቶች ብቻ የሚመራ በረራ ሊያደርግ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2016(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ ሙሉ በሙሉ በሴቶች ብቻ የሚመራ በረራ ከአዲስ አበባ ለንደን እንደሚያደረግ አስታወቀ፡፡

በረራውን ካፒቴን ቃልኪዳን ግርማ፣ ባልደረቦቿና የመስተንግዶ አባላት በጋራ በመሆን ያካሂዱታል ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው ÷ ዓየር መንገዱ ከፈረንጆቹ 2015 ጀምሮ በየዓመቱ በሴቶች ቀን ሙሉ ለሙሉ በሴቶች የሚደረግ በረራ ሲያካሂድ መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡

ዓየር መንገዱ ከዚህ ቀደም የሴቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ እንዲሁም ብቁ የሰው ሃይል በማፍራት ረገድ በርካታ ስራዎች መስራቱን ገልጸው ÷ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው ያረጋገጡት።

በተጨማሪም ÷ በአቪየሽኑ ዘርፉ የሴቶች ተሳትፎ እንዲጎለብት በማድረግ ረገድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ አረጋግጠዋል።

በታሪኩ ወልደ ሰንበት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.