Fana: At a Speed of Life!

ከ264 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ264 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዙን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ከየካቲት 15 እስከ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ባደረገው ክትትል ነው 195 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር የገቢና 68 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር የወጭ የኮንትሮባንድ እቃዎች የያዘው፡፡

ከተያዙት እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሃኒት፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ አደንዛዥ እጾች፣ የመኪና መለዋወጫ፣ የምግብ ዘይትና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

የገቢ እና የወጭ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር አዋሽ፣ ጅግጅጋ እና ሞያሌ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ቀዳሚውን ስፍራ እንደሚይዙ የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

ኮንትሮባንዱን ሲያዘዋውሩ የተገኙ ስምንት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.