Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል ማህበረሰብ ተኮር ሥርዓተ ምግብን ማሻሻል የሚያስችሉ ፕሮጀክቶች ይፋ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል የጤናና አገልግሎትን እና የማህበረተሰብ ተኮር ሥርዓተ ምግብን ማሻሻል የሚያስችሉ ሶስት ፕሮጀክቶች ይፋ ተደርገዋል።

ፕሮጀክቶቹ የጤና ሚኒስቴር ተወካዮች፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎችና አጋር አካላት በተገኙበት ነው ይፋ የተደረጉት፡፡

በአምስት ዓመታት ውስጥ ለሚተገበሩት ፕሮጀክቶቹ 154 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር በጀት መመደቡ ነው የተገለጸው፡፡

የጤና ሚኒስቴር ተወካይና የሰቆጣ ቃል ኪዳን ፕሮግራም ሃላፊ ዶ/ር ሲሳይ ሲናሞ እንደገለፁት÷ ለጤናና ለሥርዓተ ምግብ ችግሮች ተጋላጭ የሆኑ ዜጎች ድጋፍ እንዲያገኙ ከባለድርሻ አካላት በትበብር እየተሰራ ነው።

ፕሮጀክቶቹ በክልሉ በ44 ወረዳዎች ተግባራዊ እንደሚደረጉ የተናገሩት ደግሞ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አማኑኤል ሃይለ ናቸው።

የክልሉን የጤና አገልግሎት መልሶ በመገንባትና ሥርዓተ ምግብን በማሻሻል የትግራይን ህዝብ ተጠቃሚ ያደርጋሉ ማለታቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በዩ ኤስ ኤይድ ኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ ሃላፊ ጆናታን ሮዝ በበኩላቸው÷ፕሮጀክቶቹ በተለይ የእናቶችና ህፃናት ጤናን ለማሻሻል ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸው ተናግረዋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.