Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ኀብረት አስፈጻሚዎች ምክር ቤት 22ኛ ልዩ ስብሰባ ተካሄደ

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ኀብረት አስፈጻሚዎች ምክር ቤት 22ኛ ልዩ ስብሰባ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

ልዩ ስብሰባው በቀጣዩ ዓመት ለሚደረገው የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ከፍተኛ አመራር ምርጫ ዝግጅትን አስመልክቶ የቀረበውን ሪፖርት ተመልክቷል።

የሞሪታንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ መሃመድ ሳሌም ኦሉድ (ዶ/ር) በመድረኩ እንዳሉት፤ የኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮች ምርጫ አፍሪካ በሰላምና ደኀንነት እንዲሁም ዓለም አቀፍ ተፅዕኖ በመፍጠር ረገድ የሚኖራትን ሚና የሚያሳድግ ሊሆን ይገባል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ምርጫው የህብረቱን ታማኝነት በማስጠበቅ የተቀመጡትን የመመሪያ መርሆችና ደንቦችን በማክበር ለኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራር ቦታዎች መካሄዱን ማረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑን ማስገንዘባቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.