Fana: At a Speed of Life!

ተገቢ ያልሆነ የንግድ ውድድር በፈጸሙ ነጋዴዎች ላይ ከ10 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ ቅጣት ተላለፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ተገቢ ያልሆነ የንግድ ውድድር በፈጸሙ ነጋዴዎች ላይ ከ10 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ የገንዘብ ቅጣት መተላለፉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ ባለፉት 6 ወራት የሌላውን ነጋዴ ምልክት በአሳሳች ሁኔታ በመጠቀምና ሆን ብሎ ስለተፎካካሪ ነጋዴ የተዛባ መረጃ በማሰራጨት የተወዳዳሪ ነጋዴ ጥቅም ላይ ጉዳት ባደረሱ ነጋዴዎች ላይ ነው ቅጣት ያስተላለፈው፡፡

በዚህም መሰረት በሁለት ነጋዴዎች 10 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ የገንዘብ መቀጮ እንዲከፍሉ መወሰኑን በሚኒስቴሩ የፀረ ውድድርና የህግ ጥሰት መከላከል ዴስክ ሃላፊ አቶ ጌትነት አሸናፊ ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ 739 ሺህ ዋጋ ያላቸው ከንግድ እቃ ጉድለት ጋር በተያያዘ የቀረቡ የሸማች አቤቱታዎችን በመቀበል የከፈሉት ገንዘብ እንዲመለስላቸው ለጠየቁ ሸማቾች እንዲመለስላቸው ተደርጓል ብለዋል፡፡

እንዲሁም ጉድለት ያለበት የንግድ እቃ በሌላ ትክክለኛ የንግድ እቃ እንዲተካላቸው ለጠየቁ ሸማቾች በፍላጎታቸው መሰረት እንዲቀየርላቸው መደረጉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

ጉድለት የተገኘባቸው እቃዎችም ፍሪጆች፣ ቴሌቪዥኖች፣ የልብስ ማጠቢያ ማሽኖች፣ ፋይል ካቢኔቶች እና ሶፋዎች መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

ሃላፊው ሕብረተሰቡ በግብይት ላይ የሚፈጠሩ የሸማች መብት ጥሰቶችን በአቅራቢያ ለሚገኙ የንግድ መዋቅር ተቋማት ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.