Fana: At a Speed of Life!

ናይጄሪያውያን ባለሃብቶች አውሮፓ ውስጥ የእግር ኳስ ክለብ ባለቤት መሆን ጀምረዋል ተባለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ናይጄሪያውያን ባለሀብቶች አንዳንዶቹ በአውሮፓ ውስጥ የእግር ኳስ ክለቦችን መግዛት በመጀመራቸው በዓላም ታሪክ ስማቸውን መፃፍ መቻላቸው ተነግሯል፡፡

ናጄሪያውያኑ በፖርቹጋል ሁለት የእግር ኳስ ቡድኖች ሲኖራቸው አንዱ ደግሞ በዴንማርክ አንድ ቡድን እንዳለው ይፋ የተደረጉ መረጃዎች አሳይተዋል፡፡

ናይጄሪያውያን የስፖርት ደጋፊዎች በመሆናቸው የስፖርት ንግድ ስራም በናይጄሪያ ለባለቤቶች እና ለባለድርሻ አካላት ጥሩ ትርፍ እያስገኘ መሆኑ ተነግሯል፡፡

በአውሮፓ የእግር ኳስ ክለቦችን በተሳካ ሁኔታ የገዙ ናይጄሪያውያን ቢሊየነሮችን በተመለከተ የአፍሪካ ፋክት ዞን በትዊተር ገፁ ዝርዝራቸውን አውጥቷል።

ኩንሌ ሶናሜ ከነዚህ ናይጄሪያውያን ባለሀብቶች ተጠቃሹ ሲሆኑ፤ የፖርቹጋል እግር ኳስ ቡድን ሲዲ ፋይረንስ ባለቤት ነው።

ሶናሜ በፖርቹጋል 2ኛ ዲቪዚዮን ላይ የሚገኘውን ፋይረንስ እግር ኳስ ቡድንን ዋና ባለ አክሲዮን ሆነው ከገዙ በኋላ በአውሮፓ የእግር ኳስ ቡድን ባለቤት ለመሆን መብቃታቸው ተገልጿል።

የፔይስታክ ተባባሪ መስራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት ሾላ አኪንላዴ ደግሞ በዴንማርክ አርሁስ ፍሬማድ የተባለው ቡድን ከፍተኛ የአክሲዮን ድርሻ ባለቤት ናቸው፡፡

የናይጄሪያው ቴክ ጉሩ በዴንማርክ ሊግ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚጫወተውን ዳኒሽ ቡድንን 55 በመቶ አክሲዮን በመግዛት ከፍተኛ የአክሲዮን ድርሻ ባለቤት መሆናቸው ተገልጿል።

ኔካ ኤዴ የተባሉት ነጋዴ ደግሞ በአውሮፓ የእግር ኳስ ክለቦች ባለቤት በሆኑ ናይጄሪያውያን ዝርዝር ውስጥ ብቸኛዋ ሴት ሲሆኑ፤ የፖርቹጋሉ ሉሲታኖ ጂናሲዮ ክላቤ ቡድን ባለቤት መሆናቸው ተነግሯል፡፡

ኔካ ኤዴ 110 ዓመት ዕድሜ ያስቆጠረውንና በፖርቹጋል 3ኛ ዲቪዚዮን የሚጫወተውን ቡድን በፈረንጆቹ ሰኔ 2020 እንደገዙት መገለፁን የሌጂት ዘገባ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.