Fana: At a Speed of Life!

የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ከ139 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የእርሻ መሳሪያዎች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ከ139 ሚሊዮን በላይ ግምት ያላቸውን የእርሻ መሳሪያዎችን በእርሻ ስራ ለተሰማሩ የሰራዊቱ ክፍሎች ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

የመከላከያ ሠራዊት በምግብ አቅርቦት እራሱን እንዲችል በመንግስት በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የመከላከያ ክፍሎች በሚገኙበት አካባቢ ከመስተዳድሮች ለልማት የሚውል የእርሻ መሬት በመረከብ በግብርናው ዘርፍ ላይ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡

ይህንኑ ሥራ ለማበረታታት የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ የቆየው የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን፤ በዛሬው እለትም ከ139 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን የእርሻ መሳሪያዎች ድጋፍ አድርጓል፡፡

በዚህም 20 ዘመናዊ የእርሻ ትራክተሮች፣ 17 ማረሻዎችና ስምንት መከስከሻዎች ሲሆኑ፤ ለደቡብ፣ ማዕከላዊ ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ለምዕራብ እና ለሰሜን ምስራቅ እዞች መሳሪያዎቹ ተሰጥተዋል፡፡

ለምርጥ ዘር፣ ለማዳበሪያ፣ ለጸረ አረም እና ለሌሎችም ግብዓት መግዣ የሚሆን ከ6 እስከ 14 ሚሊየን ብር በጀት ለእያንዳንዳቸው በብድር መልክ ለመሥጠት መታቀዱም ተመላክቷል፡፡

በተጨማሪም ፋውንዴሽኑ የሰራዊቱ የእርሻ ስራ እንዲቀጥል ከግብርና ሜካናይዜሽን ኢንስቲትዩት ጋር መተባባር 20 የትራክተር ኦፕሬተሮች እና 20 የእርሻ ትራክተር የጥገና ሙያተኞች ስልጠና እንዲወስዱ እያደረግን መሆኑን የመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.